Get Adobe Flash player
ሎግ ኢን ሜኑ
ይምረጡ/ፖል
አገልግሎት አሰጣጥ
 

waghimra፣Ziqula

በዋግኽምራ ብሄረሰብ አስ/ር ዞን በዝቋላ ወረዳ የሻደይ በዓል አከባበር ምንነት ለማወቅ ይህን ጽሁፍ ያንብቡ

shadey

ሻደይ ማለት በኸምጣጞ ለምለም ማለት ሲሆን ሴቶች የሚታጠቁት  ቅጠል  መሰሉ ቅጠል ነዉ፡፡ የሻደይ ታሪካዊ  አመጣጥ ስንመለከት ደግሞ ሀይማኖታዊ  ይዘት  ያለው  ነው፡፡ ይህም  በመሆኑም  ከመቤታችን  ቅድስት ድንግል ማሪያም   የእርገት  ባዓል ጋር  የተያያዘ  እንደሆነ የሃይማኖት  አባቶችና  የአከባቢው  ነዋሪ  የሆኑ  አዛዉንቶች  ይናገራሉ እንጅ ማንኛዉም ማህበረሰቡ ስለ ሻደይ ጨዋታና አከባበር  ምንም አይነት  እዉቀተና  ግንዛቤ ከምን  እንደመነጨ እዉቀቱ  የላቸውም ከአንዳንድ አባቶችና አዛዉንቶች በስተቀር፡፡ ‹‹‹በዓሉ በልጃገረዶች ዘንድ ተወዳጅ የሆነዉ በሄዋን ምክንያት የተዘጋዉ ገነት በእመቤታችን አማካኝነት መከፈቱ ነዉ፡፡እንዲሁም መመኪያቸዉ ስለሆነች ልጃገረዶች በአሉን ያከብሩታል፡፡ድንግልናቸዉን አደራ የሚሉበት በእርእሱ ነዉ፡፡ካለ በኋላ በዓሉ ከኖህ ዘመን ልምላሜ ተምሳሌት አድርገዉ እንደሚወስዱ አባቶ እንዳሉ ገልጾ እመቤታችን በኖኅ መርከብ እንደምትመሰል አስረድተዋል፡፡ተምሳሌቱንም ሲያብራራ ሰዉ ልጅ በኖህ መርከብ ከጥፋቱ እንደዳነ ሁሉ በልጇ ያመነና በእርሷ የአምላክነት የተማጠጸነ ሁሉ ይድናል ፡፡በዚህም በኖህ መርከብ ትመሰላለች ሲሉና አክለዉ አሸንዳ ቅጠል የኖህ መርከብ ያመጣችዉ የለምለም ቅጠል ተምሳሌት ያብራራሉ ልጃገረዶች ቅጠሉን  እሽከረከሩ መጫወታቸዉነወ /እያሸበሸቡ/ደግሞ እመቤታችንን ያሳረጉት መላክትን ይዘክራሉ ብለዉ በጥቅሉ ሻደይ የባህል አከባበሩ ከቅድስት ድንግል ማሪያም ጋርም ይሁን ከኖህ መርከብ ጋር ተዛማጅነት እንዳለዉ መመልከት ተችሏል፡፡ምንጭ ሻደይ ወንዝ አይፈሬ መጽሄት›››፡፡የሻደይ  ባህል  ጨዋታ ቋንቋ አመጣጥ ስንመለከት ደግሞ  ከማንም  ቋንቋ  የተወረሰ ሳይሆን  የራሷ  የኢትዮጵያ  የመጀመሪያ  የሰው ልጅ  መግባቢያ  ከሆነው  የግዕዝ ቋንቋ  የመጣ መሆኑ እና  ይህም የግዕዝ ቋንቋ  በመጥፋት ላይ  ያለ   እና  እንዲሁም  የኦርቶዶክስ  ተዋህዶ  ክርስቲያን የቤተክርስቲያን  ቋንቋ ሁኖ የሚገኝ ነው፡፡  ምክንያቱም  የቤተክርስቲያን  ፅሁፎች  አባቶች በግዕዝ  ፅሁፍ ነው የሚጠቀሙት፡፡‹‹ሻደይ በዓል አከባበር  በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በመላዉ አለም ካሉት በዓላት ሁሉ በዕድሜ ትልቁና የመጀመሪያዉ ቅዱሳት በዓል ነዉ፡፡››  ሰለዚህ ይህን መሰረት በማደረግ   ይህ ባህላዊ ጨዋታ ሰርዓቱ  የመጣው  ከግዕዝ ቋንቋ  መሆኑን ያመለከታል ፡፡ ይህ  ባህላዊ ጨዋታን ስንመለከት  የሚከበረው በወራዊ  ንሀሴ 16 ቀን ሲሆን  ተጫጨዋቾቹ  ግን  ዝግጅት የሚጀምሩት  በዓላቱ  ከመድረሱ በፊት  ከእያሉበት ሰፈር እየተሰባሰቡ  ሰለ  በዓላቱ አከባበር  አንዳንድ  ቀልድና  ቁም ነገር  አዘል  እያነሱ  ይጨዋወታሉ፡፡ ከዚያም  በዓላቱ  ቀን  ከመድረሱ በፊት ከአምስ ቀን ባላነሰ ጊዜያት በአንድ  ላይ  በመሰባሰብ  ቁጥራቸው  ይህን  ያህል  ተብሎ  ባይወሰንም  በየቡድን  በመሆን  ሴቶች ሆኑ ወንዶች  ከአባቶቻቸው  በትውፊት  የወረሱትን  ከትውልድ  ትውልድ ሲወርድ  ሲዋረድ  የመጣውን ባህል  ያለምንም  ስልጠና እና እገዛ  በልምድ  እያንዳንዱ ቀበሌዎች  በየሰፈራቸው እና በየጎጡ የባህሉን ጨዋታ  አብረው በድምቀት  እያከበሩ  ከዘመን ዘመን  ይሸጋገራሉ፡፡   ይህ  የሚሆነው  እንደተባለው  በዓላቱ  ሲደርስ በድራሩ የሻደይ   ቅጠል ሻደይ የሚባለውን  ለመቁረጥ ሲሄዱ ሜዳ ላይ እንደዚህ አይነት  ዜማ አቨቫየንሰ አቨቨጞ የዲጊል እኩች ቢቋለተጞ

shadey

 

እፈ አቨቫ  አቨቫየ

እፈ አቨቫ  አቨቫ አቨቫየ

ጥዋሰ መልጎመ አቨቫየ

ቃጠ ድኩትደ  አቨቫየ

ቓሊሰተ  ተትርኩች አቨቫየ

ሸገጝረ ባህልድ አቨቫየ

ቦፊ አልቨድ ሲትር አቨቫየ

መልጎምድ ፃቨር  አቨቫየ

ሻደይቱ ሻፀ  አቨቫየ

ይወዝሳ ከምትር  አቨቫየ

ቓሊሰተ ተትርኩች  አቨቫየ

ጝር ኸምጠ ባህልድ አቨቫየ

በማዜም  ሻደያቸውን  እየቆራረጡ ይጨዋወታሉ፡፡  ከዚያም  ቆርጠው ከተመለሱ  በኃላ  የቆረጡትን ሻደይ  መሰራት የሚችል ማንኛዉም ሰው ይሰራና ያአንን  ሻደይ ሴቶች  ከወገባቸው ዝቅ ከዳሌቸው  ከፍ  አድርገዉ በመታጠቅ በዕለቱ ቀን ስርዓቱ የሚከበረው  ህግና ደንቡ ደግሞ ከቤታቸው ተነስተው ወደ ቤተክርስቲያን  በመሄድ  ሲሆን ወደ ቤተክርስቲያን  ሲሄዱ እና ከቤተክርስቲያኑ ዉስጥ ማንኛዉም ከአጥር ግቢ ያለ አንድ ላይ በመሆን እንዲህ                           ሻደይ ሻደይ ሻደይ

ደውልሽ ኻየተ ኻየተ ጊግቨተ ኻየተ

ሻደይ አቨቨ እሸደየአ

ሻደይ  አቨቨ እሻደይ

እፈር አቨቨያ  እፈር አቨቫየ

እፈር  አቨቫየ  እፈር አቨቫ

እፈር  ክርጞ ክረጞ እፈር  አቨቫ

ይጞኩ የንታታየ  እፈር አቨቫ

ንጭኩኑ ክረጞ እፈር አቨቫየ

ጛቕመን የንታታየ እፈር አቨቫ

ወጭ ፈረ አቨቫ እሆ

አቨቫየ አፈረ አቨቫየ

አይነት  ጥሩ ጥሩ  ጣዕመ ዜማዎችን  እያዜማሉ፡፡  ቤተክርስቲያን  ከአዜሙ   በኃላ ወጣቶች   ከታጠቁት ሻደይ ቅጠል ጫፍጫፉን በመቆራረጥ  ይጠላሉ፡፡  ይህም የሚጥሉት  የሻደይ ቅጠል  ጨለማው ዘመን  አልፎ  ብርሀናማ  ዘመን ደረስን    የማለት  ተምሳሌት  ነው፡  ይህን  ሰርዓት  ከፈፀሙ  በኃላ  ወደ ሰፈራቸው በመመለስ  በበዓሉ  የሚስፈልጋቸውን  ለማግኘት  በዜማ

ሎዉሚለወ ሎዉሚለወ ሽወር ኸነረ

ሎዉሚለወ ሎዉሚለወ ሽወር ኸነረ

አይሎሚለው ኸደር  ማፅወ ለወ

አይሎሚለው ኸደር  ማፅወ ለወ

አይሎሚለወ ሽዉርኹነለወ

አየደሞሚነወ  ታይም ጎፈሪው

እንዲህ እያሉ  በመግለፅ  እንደ  ድቄት ፣ ቅቤ ፣ በርበሬ፣ ብር፣ ሳንቲም የመሳሰሉትን ይሰበሰባሉ፡፡  በዚህም አጋጣሚ  ወንዶች  ሴት  ጓደኛ  የሚመርጡ  ሲሆን የሚሰበሰቡት  በየቤቱ እየዞሩ  እና እንዲሆም በመንገድ  ላይ የሚያገኘቱን   ሰው ከመኃል  በማሰገባት   በመክበብ  እንዲህ በማወደስና በማስደሰትመውደድ ቺልው  መውደድቺልወው

መውደድቺልው  መውደድ

ፅቃ ሸልጝጊ  መወደድ

ጅቦሰ ጭልቕወ መውደድ

ጉየወ ብሸቱ መውደድ

ሰነደል ጥውወ መወደድ

ሸደይ አቨቫ ሻደይ አቨቫ

ደቫከ ተርች  ካባ ሲትር

እፈ አቨቫ  ሻደይ አቨቫ

እፈ አቨቫ  አቨቫ  ሻደይ አቨቫ

ፃርፃርሸው   በውገተ  ሸደይ አቨቫ

ኸረየኩ በጀወድየን  ሻደይ አቨቫ

ቅድስ  ገብሬል ቃየው  ሻደይ አቨቫ

ኸየወደቨረድየነ  ሻደይ አቨቫ

ይልል  ልል ቅጥረሽ ቅጢርና አምረይሰቨአነ

ያን ክኘ ቃጥልጭር  ይልል እስክስ እስክስ

እያዜሙ  ይጠይቁታል  ያለውን  ከሰጠ በኃላ  ወይም  አለመኖሩን  ከገለፀ አምር ንጭስ ችጞዝነ ትርጉሙ  የከርሞ ሰው ይበላች ብለዉ ይመርቃቸዋል ፡፡እንዲሁም የአንድ ጎጥ ወይም ቡድን የሚያጥላሉበት ዜማ የለም ነገርግን የማይወዱትን ሰው የሚያጥላሉበትና የሚሰድቡበት ሁኔታ አለ እሱም  እንዲህ  እያሉ   ድኃረ ንጭር  ውር ፃበነው  ኒግድን  ሆነው

ንጭር ግልወ ውር ፃበነው

ግንድ መውሰነው

ጝድሪ ኾስር በርሽ የጓ

የን ኽርተዝ ጊዜ ቲስመመኩን የን

ሲሉ በመስደብና ማንቋሸሻቸዉን ይገልፃሉ፡፡

እንዲሁም የሚወዱት ወንድ ልጅን ለማሞገስ እንዲህ ሲሉ በዜማ

እትመ አየውመ እንተመ አየወመ

ደሸኩንመ  ድሻርም

ቸለኩንመ  ቸላርመ

እንጎመ እየውም

እጎመ አየወም

አይሎሚለወ አይሎሚለወ  ህደረ ማፅወለው

አይሎሚለወ ህደረ ማፅወለወ

ሽወረለወ ህደር ማፅወለወ

ኰሊ ለወ ህደረ ማፅወለወ

አይሎሚለወ ሎሚለወ  ሽዉር ይራጙ ለወ

አይሎሚለወ ሽወረ ይራጙ ለወ ብለዉ ይገልፃሉ

በተዘዋዋሪ የሴቷን ዉበቷንና ሙሉ ገፅታዋን፤ማሞጎስ፤ጠንካራና ደካማ ገፅታ ለመግለፅ በእንዲህ አይነትእንድችም  ይነኩን እንድችም ይነኩን

አውርድም  ይነኩን ሽኳርድም ይነኩን

ጉትቸም ይነኩን  ሚስቅልድም  ይነኩን

ድሪድም  ይነኩን  ጥልፍድም  ይነኩን

መልጓምድም  ይነኩንድኩተድም  ይነኩን

ቦፌድም ይነኩን

ጻሌድም ይነኩን

ላይኒዑስ ዊንቸ ጝሪም ላሊበላ ፊትርኩች በማለትሙሉ ገፅታውንና ዉበቷ እንዲህ ሲሉ ሲገልፁ፡፡

ማስክቲቲ እህ

ማስክቲቲ እህ

ዘጎይ ክምትይ እህ

ሰቁጠ ክቢቲ እህ

ቀሰነ በዊል እህ

ወንጨ ለምርቲ እህ

ዝቅጭር ይራጙ እህ

ስርብር ይርክርቲ እህ

ሻፍረ ጅጢል እህ

እኹረሸውድ እህ

አወልፊሩ እህ

ስምር ፊሩ

ወረድ ነሰጠ  እህ

መትባን ነስጠ እህ

አወጝኘሰ እህ

ያንጝወነሰ

እህ ያላትን አስተሳሰብ አመለካከት በጠንካራ ጎን ሲያነሱ ደካማ ደግሞ እንዲህ

ጣቨ ቕረጞ  እህ/2/

አስጥን  ከታቑርት እህ

ግብ ሊቅመቸ እህ

አለፉ ወነ እህ

ለውመ ክወነ እህ

አለፍ ቢትው እህ

ክለፈድ ቢቱ እህ

ጞጝም ጉልምቱ እህ

ዲባርመ ዊንዱ እህ

ውርቃልዳኝ  ዊንዱ እህዜማ ያዜሙ ደካማ ጎኖችን ያነሳሳሉ፡፡ የሚኖሩበትን ወረዳዉቸዉን ወይም ቀበሌያቸዉን ቢሆንም በእንዲህ አይነት ዜማ እያነሳሱ አያወዳደሱ ያሸበሽቡላታል ሻደይ አቨቫ ሻደይን አቨቫ

ዲቨከ ተርች ካባ ሲትር

እፈ አቨቫ አቨቫ ሻደይ አቨቫ

እፈ አቨቫ አቨቫ ሻደይ አቨቫ

ፃርፃረሸወ በውገተ ሻደይ አቨቫ

ኸረየኩ  በጀወድየን  ሻደይ አቨቫ

ቅድስ ገብሬል ቃየው ሻደይ አቨቫ

ኸየወዲቨረድየነ  ሻደይ አቨቫ

ይልልል ልል  ቅጥረሽ ቅጠርና አምረይስቨ አና

ያንጞኘ ቃጥልጭር ይልል እስከስ እስክስ

ያሞጋግሳሉ  ለተከታታይ ቀን አብረዉ ከሰነበቱ በኃላ በሻደይ የመጨረሻ ቀን ይህን አይነት ዜማ በማዜም የሚናፍቋትን አመት በደስታና በልልታ

አቲነትኝ ሊግዘናነ ደበደበደበ

ቢርብረትጞ ስርናነ

ፍርጣጠትጞ ዲነናነ

ሰረኩን  ቖብዘኩን

ሰረኩን  ቖብዘኩን

ኪረእጅኝ ይረ ሊግዘው

ኪረእጅኝ ይረ ሊግዘው

በማለትያጠናቅቃሉ፡፡ እንዲሁም በመጨረሻም ቀን የሰበሰቡትን  ዱቄት  ደቦ  ወይም በተለምዶ አስኩር እየተባለ የሚጠራዉን እየጋገሩ  በቅቤያቸው እና  በበርበሪያቸው የፈረፈሩ ይበላሉ፡፡ይሰነበቱበት እና  እንዲሁም  ለተከታታይ  በአንድ ላይ በቆይበት ቀን መጨረሻ ለከርሞው  ያድረሰን  እያሉ እየተመራረቁና  የከርሞያቱን  ቀን  እየናፈቁ፤  እያወደሱ፤  እያሞገሱ  ለቀጣይም  ትውልድ  እንዲሰተላለፍና  እንዲናፍቁ  ሰሜታቸውን  እየሳቡ  ይለያያሉ፡፡ለሶስት እስከ አራት ቀን ቆይታ የሰበሰቡትን ብር እና ሳንቲምም በአንድ ላይ በማጠራቀም በአንድ የቡድን መሪ አማካኝነት ለቤ/ክ ያስገባሉ፡፡ይህ  ባህላዊ  ጨዋታ  ዛሬ  እንደለ  ከሰፈር አልፎ  ወረዳና ዞን  እንዲሁም   በአገር ደረጃ  እየታወቀ  ሲመጣም  ሰርዓቱም  እንደለ ቢሆንም  የተወሰነ  ለውጥ  ተደርጎ   ከቅርብ   ወዲህ  በወረደና  በዞን   ደረጃ  በ3  ቡድን  በመከፋፈል  ማለትም  ህፃናት፣ ወጣቶች እና  እናቶች  ተብሎ  በቁጥር  ተወሰኖ  እየተከበረ  ሲሆን  በብዛት  የዚህ  ባህላዊ  ጨዋታ  የሰራ  ድርሻውን   የሚይዙት  በብዛት   ሴቶች  ሲሆን  ይህ  ሲባል  ደግሞ   ወንዶች  ምንም  አይነት  ድርሻ የላቸውም    ማለት  አይደለም  በአጠቃላይ  በዚህ  መስፈርት  ከተከፋፈለ  በኃላ ሰለ  ጨዋታው  ሁኔታ ማለትም  በወራዊ  ነሀሴ  16  ቀን  የሚከበረውን  ባህላዊ  ጫዋታ  ከመድረሱ  በፊት  በእያንዳንዱ  ቀበሌ  መልማዮችን  በመላክ  የተለያዩ  መሰፈርቶችን  በመጠቀም   ከመለመሉ  በኃላ  ለወረዳ  ያለፋትን  ከንሀሴ  16  ቀን  በፊት    ቀድመው  ወረዳው  ድረስ በመምጣት  ቅደመ  ዝግጀት  ያደርጋሉ፡፡ ይህን   ቅድመ  ዝግጀት  የሚያደረጉት   ያላቸው ችሎታ  እንዳለ  ሁኖ  ሌላ  ተጨማሪ  ማስተካከያና  ማብራሪያ  በባለሙያ ድጋፍ እየተደረገ  እንዲሁም  ስልጠና  እየተሰጠ  ይሰነበታሉ፡፡ ስልጠናው የሚሰጥበት  ምክንያት  ካሉት  ስልጠኞች  የተለየ  እንቅስቃሴ  ወይም   ከባህሉ  ወጣ  ያለውን   ለማስተካከል ነው፡፡  ይህ  ስልጠናና  ማስተካከያ  ከተሰጣቸው በኃላ   ለባህሉ  የሚያሰፈልጉና ሊያደምቁ የሚችሉ  የተለያዩ  የባህል አልባሳቶችን  ጌጣጌጦችን  ቀሚስ፣ድሪ፣ድኮት፣ የብር መስቀል  ኩል፣ማርዳ፣ጉትቻ፣ የሻድያ  ወ.ዘ.ተ የመሳሰሉትን  ማስዋቢያ ያዘጋጃሉ  ከዘጋጁ በኃላ ደግሞ   ለፀጉራቸው እንደ እንደየዕድሜያቸው  ጋሜና ቁንጮ፣ ስቅለሽ እና ስውዱላ  የተባሉ  የፀጉር ሰሬት  አይነቶችን  በመሰራትና  ሰሬታቸውን ይበልጥ ለማድመቅና ውበት  ለመሰጠት በስሬታችውና  በግንበራቸው አከባቢ  ከብር፣ ከመደብ  እና  ከተለያዩ አብረቅራቂ  ነገሮች  የተሰሩ እንደ ወለባ፣ መርፌ ቁልፍ እና  አሽክት  የተባቡ ጌጣጌጦችን በመጠቀም  ሰሬታችውን  በቅቤ ያሰውባሉ ወንዶች በድርሻቸው ደግሞ ጀበረባሬ፣ፈራድ፣ መጥረቢያ፣በትረ፣በልባል፣ቅል ወ.ዘ.ተ የመሳሰሉትን  ማሰዋቢያ  ያዘጋጀሉ፡፡ እንዲሁም  ፀጉራቸውን  እንደየድርሻው  ወይም  እንደየዕድሜያቸው ቁንጮ  በማውጣት፣ ፀጉራቸውን በማበጠረ፣ ማሰዋቢያ  ለፀጉራቸው እንደ ሚደ ለጥረሳቸው ደግሞ መፋቂያን በመያዝ የእራሳችውን  ድርሻ ይወጣሉ ከዚያ የሚያስፈልጋችውን ነገር ከአሟሉ በኃላ በዕለት ቀኑ ማለትም በወርሃው ንሀሴ   16 ቀን ሴት 30—36 ወ 2—4 ድ 32–40 ዝግጁ ሆነው ባህላቸዉን ለህዝብ እይታ  ለማቅረብ በተዘጋጀላቸው ቦታ በመገኘት  ሰራቸውን   በልልትና ሆታ በድምቀት ከላይ የተጠቀሱትን ጣዕም ጣዕም ያላቸውን ዜማ እያዜሙ ሴቶች ሻደያችው ከወገባቸው ዝቅ ከዳሌያቸው ከፍ አድረገው  በመታጠቅ  የሚናፍቋትን  ቀን ሴቶች   ከመኃል ወንዶች  በጎን  በመሆን እያሸበሸቡ  ሞራል  እየሰጡ ሴቶችን  እያበረታቱ ጣዕመ ዜማቸውን  እየተቀባበሉ በዓሉን  በዓል  እያደረጉ  ለህዝብ  እይታ ያቀረባሉ፡፡ በዚህ ሰዓት ስርዓቱ ከሰፈር  ወይም  ከቀበሌ እተለየ  መጣ  የተለየበት ዋና ዋና ምክንያት በአጠቃላይ በቁጥሩ ውስን መሆኑ  የሚያቀረቡት  ሰዎች  የጉልበት ላብ ወይም ክፍያ  ገንዘብ ሰለሚከፈላቸው  የሚከፈበችውን  ገንዘብ ከራሳቸው ጥቅም  ውጭ ለምንም  አይነት  አገልግሎት  አለማዋላቸው፣ የሴቶች ቁጥር በዝቶ የወንዶች  ቁጥር ዝቅ ማለቱና በባለሞያ ስልጠናና እገዛ መደረጉ ልዩነቶች ሲሆኑ የቀበሌው ወይም  የሰፈሮች  ልጆች  ግን  በላብ  ያገኙትን  ገንዘብ  ለቤ/ክ ገቢ ያደርጋሉ እንዲሁም ምንም አይነት ስልጠና አለማድረጋቸዉ  ይህ  መሰል  ልዩነት   በመኖሩ የባህል  ለውጥ  እና የመበረዝ ሀይል  እንዲኖረው  እያደረገ በመሆኑ  ይህ  ጥንቃቄ  ተደርጎበት  ሊሰራ  ይገባል፡፡ እንዲሁም  ለትውልድ  ለማሰተላለፍ  ይረዳ  ዘንድ  ከፍትፍቱ ፊቱ  እንዲባል  አቀራረቡ  ሰርዓት  በባህዊ ባህላዊ  የሚሸቱና  የሚገልፁ  መሆኑን መዘንጋት የለባቸውም፡፡ //ሻደይ ስርዓቴ ሳይበላሽ ድረሱልኝ ብላ እየጮኸች ስለሆነ// ፡፡

ማህበራዊ ጠቀሜታ

ይህ የሻደይ  ባህል  ስርዓት ጠንካራና  ጥሩ የሆኑ ታሪክ  ያለው ሲሆኑ ካሉትም  ጥሩ  ጎን

  • ጥሩ የሆኑ ማህበራዊ  ግንኙነት እንዲኖር ያደርጋል
  • በቂ የሆነ  ማህበራዊ  ግንኙነት  የሚመሰረቱበትና  ዕውቅትና ጥበብ  የሚያገኙበት ነው
  • ከሰፈርና ቀበሌ  አልፎ  ከወረዳና ዞን  እንዲሁም  አጎራባች  ወረዳዎች  ጋር  ፍቅርን  የሚመሰርቱበት እና የሚሰተዋወቁበት ነው
  • በሰፈሩና በቀበሌዎች ያሉት ሰዎች  የተጠሉት  የሚታረቁበት እና የማፈቃቀሩበት  ባህል ነው
  • ለቀጠይ ትውልድ የሚያሰተላልፍበት   ወይም  የማይችሉት  ከሚችሉት  ለመቅደት  የሚናፍቁበት ባህል  ነው፡፡

ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ

ይህ የሻደይ ባህል  የሚያሰገኘው ገቢ  ከፍተኛ ነው  ከነዚህም መካከል

  • የሻደይ ባህል  ተጨዋቾች  የሰበሰቡትን  ገንዘብ   በአንድ  ላይ  በማድረግ  ለቤ/ክ መሰጠታቸው  ለቤ/ክ ሰራ  ማሰከጃ  መዋላቸው
  • በባህሉ የሰበሰቡትን እህል ውኃ የሚዘጋጀበት  ጊዜ  ከእራሳቸው ተርፎ  ለእኔ ቢጤ(ለነዳያን)  መሰጠት መቻላቸው
  • ለወረዳና ለዞን በሚሄዱበት ጊዜ  የቀን  ዉሎ አባል  ክፍያ ማገኘት መቻላቸው
  • የወረዳዉን ባህላዊ ገዕታ ከማሳደግ አኳያ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል

ፖለቲካዊ  ጠቀሜታው

ይህ  የሻደይ  ሰርዓት  በዝቋላ ወረዳ  ማህበረሰብ የተለያዩ  የማሳመን  የማይወዱትን  ሰው  ለማጥላላትና  ለመስደብ  የሚጠቀሙት  ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ጋር  ሲነጣጠር በጣም  በጣም  ከፍተኛ  አድናቆት  የሚችር ነው፡፡ ይህ  ሲባል  የባህል  ተጨዋቾች   ግለሰቦችን  (ጓደኞቻቸውን) ለማግባባት፤ ለመቀዋወምና  ለመተቸት የሚጠቀሙት የንግግር  ክህሎት የፖለቲካ  አቅማቸው  ምን ያህል  እንደሆነ  የሚያሳይ መሆኑ ነው፡፡

በዝ/ወ/ባ/ቱ/ጽ/ቤት በባህል ባለሙያ የተዘጋጀ